ስለ
የእኛ አገልግሎት ጌታችንንና መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማክበርና የመጨረሻ ትዕዛዙን “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ… ደቀመዛሙርቴ አድርጓቸው” (ማቴ 28፡19) ያለውን ተልዕኮ ለማሳካት ነው።
የእግዚአብሔርን ቃል መሠረት በማድረግ ጽሑፍንና የድምፅን ያጣመረ ሀብት እናዘጋጃለን።ይህ የተዘጋጀ ሀብትም ትኩረት ያደረገው በወንጌል ማዳረስና ደቀመዝሙርት ማድረግን ያጠቃልላል። ዝግጅቶቹ በሙሉ በዋናነት “ታሪክን” የማቅረብ ዘደን በመጠቅም የቅዱሳት መጻሕፍትን እውነት ይገልጣሉ።
በአሁኑ ጊዜ አምስት አይነት የትምህርት ዝግጅቶችን እናዘጋጃለን። እነዚህ የትምህርት ዝግጅቶቹም በሚዲያ የሚያሰራጩ አካላት በራሳቸው ዝግጅትና እቅድ እንዲጠቀሙ ይፈቅድላቸዋል። እኛ ትኩረት ያደረግነው ሰዎች ወደ ጌታ መጥተው አምነው እንዲድኑ ለማድረግ ነው። ይህንን የምከናወነው የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርትና የኢየሱስን ታሪኮች በሁሉም ሥፍራ ያሉ ሰዎች እንዲረዱና እንዲቀበሉ ለማድረግ በድራማና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መልክ በማቅረብ ነው። እነዚህ ፕሮግራሞች በዓለም ዙሪያ በሬድዮና በሌሎች የመገናኛ ዘዴዎች አማካይነት ይሰራጫል።