ይህ ቪድዮ ሉቃስ ስለ ናዝሬቱ ኢየሱስ ያስቀመጠልንን ምስል ያጠቃልላል። ደቀ መዛሙርቱ መቃብሩ ባዶ እንደሆነ አዩ፣ ከሞት የተነሳውን ኢየሱስንም ባገኙ ጊዜ ስለ አለም ያላቸው አመለካከት በሂደት ሙሉ በሙሉ እንደተገለባበጠ እናያለን። ሉቃስ፣ የኢየሱስ የእግዚአብሔር መንግሥት ተልእኮ ወደ ሚጠናቀቅበት ሰዓት ሲደርስ በማሳየት ይህ ተልእኮ እንዴት እንደሚቀጥል ለሚያሳይበት የሐዋሪያት ሥራ ለሚባለው ለሁለተኛው መጽሀፉ ያዘጋጀናል። #BibleProject #ሉቃስ