የክርስትና ህይወት መርሖዎች
ይህ ትምህርት መሰረታዊ የሆኑ የክርስትና ርእሶች ላይ በስፋት ያስትምራል። ይህ በተለይ ለአዳዲስ አማኞች በጣም ጠቃሚ ነዉ። በሁሉም መልኩ ለእየሱስ ክርስቶስ ስልጣን ይገዙ ዘንድ ያግዛቸዋል። በክርስትያናዊ ህይወት እንዲያድጉ እና መታዘዝን በህይወታቸዉ እንዲለማመዱ ይረዳቸዋል። ስለእግዚአብሄር እና ስለእግዚአብሄር ቃል ያላቸዉን እዉቀት ያዳብሩ ዘንድ ያግዛቸዋል። ሌሎችን በፍቅር ማገልገል ያስችላቸዋል። ቤተክርስቲያንን በወንጌላዊነት እና በደቀመዝሙርነት እንድትሰፋ ይረዳል።
-
ሞዱል 1: እየሱስ ክርስቶስ ማን ነዉ?
ይህ ተከታታይ ትምህርት ከክርስቲያን እይታ አኳያ እየሱስን እንደ ግለሰብ እና ስራዉን ያስተዋውቃል። ይህንን ለማድረግም የእርሱን ማንነት፣ ስራዉን፣ አስትምህሮቱን እና ሞቱን ግምት ዉስጥ ያስገባል። ለክርስትና እምነት እና ሃይማኖት እየሱስ ማእከሉ በመሆኑ እንድ ደቀመዝሙር እየሱስን ማወቁ ግድ ይላል። ከዚህም በላይ ክርስትናን የሚመረምሩ ሰዎች እየሱስ ክርስቶስን ምን ልዩ እንዳደረገዉ እና እኛ የእርሱ ደቀርመዝሙር እስከመሆን እና ለእርሱ ማደር ድረስ የሚያደርስን ምክንያት ምን መሆኑን ማርምሮ ማወቅ አስፈላጊ ነዉ። ተሳታፊዎችህ ከተለያየ ባህል እና የሃይማኖት ስርአት ካለዉ መሰረት የመጡ ሊሆኑ ይችላሉ። ይህም ስለእየሱስ ክርስቶስ እና ስለአስትምህሮቱ የተለያየ እሳቤ ይዘዉ እንዲመጡ ሊያደርጋቸዉ ይችላል። ወደፊት ስለሚኖራቸዉ የደቀመዝሙርነት ትምህርት ይህ ተከታታይ ትምህርት እጅግ ግሩም የሆነ መሰረት ይሰጣቸዋል። -
ሞዱል 2: ድነትን መረዳት
ይህ ተከታታይ ትምህርት የመዳንን መሰረታዊ ሃሳብ ከመመርመሩም ባሻገር አንድ ሰዉ ክርስትናን ከተቀበለ በሁዋላ በህይወቱ ዉስጥ ምን እንደሚፈጠር ይመረምራል። አንድ አማኝ ወንጌልን ዉጤታማ በሆነ መልኩ ለሌሎች ለማካፈል ይችል ዘንድ ይህንን መሰረታዊ የሆነ ትምህርት በሚገባ መረዳት ወሳኝ ነዉ። እያንዳንዱ ትምህርት ሃሳቡን ከመጽሃፍ ቅዱስ አኳያ ይመረምራል። እኒህ መሰረታዊ ሃሳቦች ላይ ዉይይት ይደረግ ዘንድ እና በህይወትህ ዉስጥ እንዴት አድርገህ ዉጤታማ በሆነ መልኩ ልትጠቀምባቸዉ እንደምትችል ለመወያየት እንዲያመች ጊዜ ይሰጣል። ይህ ተከታታይ ትምህርት አዳዲስ አማኞችን ለደቀመዝሙርነት በምናሰለጥንበት ወቅት ሃሳቡን በሚገባ ይግነዘቡ ዘንድ እርግጠኞች ለመሆን እጅጉን ጠቃሚ ሁነዉ እናገኛቸዋለን። -
ሞዱል 3: የክርስቲያን ሕይወት እና የአለም ዕይታ
ይህ ተከታታይ ትምህርት ክርስትያናዊ ህይወት ይኖረን ዘንድ እንዲያግዘን የሚያስፈልጉንን መሰረታዊ ምርጫዎቻችንን እና ልምምዶቻችንን ይመረምራል። የእግዚአብሄር ቃል እንደሚያስተምረን መኖር ማለት እያንዳንዱ ቀን የምንወስዳቸው ምርጫዎች እምነታችን ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድሩ መረዳት ማለት ነዉ። ከዛም ባሻገር ጸሎት ናድረግን መማር፣ የእግዚአብሄርን ትእዛዛት ተግባር ላይ ማዋል እና ሌሎችን ማገልገልን መማር ማለት ጭምር ነዉ ። የክርስትናን ልምምዶች ለመረዳት እኒህ በጣም ጥቃሚ ትምህርት ናቸዉ። እኒህ መሰረታዊ ሃሳቦች ላይ ዉይይት ይደረግ ዘንድ እና በህይወትህ ዉስጥ እንዴት አድርገህ ዉጤታማ በሆነ መልኩ ልትጠቀምባቸዉ እንደምትችል ለመወያየት እንዲያመች ጊዜ ይሰጣል። -
ሞዱል 4: ከእግዚአብሄር ጋር ያለን ዝምድና
ይህ ተከታታይ ትምህርት ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን ዝምድና ይመረምራል። የእግዚአብሄር ልጅ መሆናችንን ተከትሎ የሚመጣዉን በክርስቶስ የእኛን ማንነት በመረዳት ይጀምራል። ይህ ተከታታይ ትምህርት የእግዚአብሄርን ባህርያት ይመለከታል። ስለግዚአብሄር እንዴት ልንማር እንደምንችል እና የበለጠ ልናዉቀዉ እንደምንችል፣ እንዴት አድርገን ይህንን ግላዊ ዝምድና ከእርሱ ጋር ልናዳብር እንደምንችል ይመረምራል። እግዚአብሄር ያቀደልን አይነት ህይወት ይኖረን ዘንድ ራሳችንን ከእግዚአብሄር እይታ አኳያ ልንረዳዉ እና እግዚአብሄር ማን እንደሆነ ግልጽ የሆነ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል። -
ሞዱል 5: የወንጌል ስርጭት መንደርደርያ
ይህ ተከታታይ ትምህርት ተሳታፊዎች ወንጌልን ዉጤታማ በሆነ መልኩ ለሌሎች ማካፈል ይችሉ ዘንድ ማዘጋጀት ነዉ አላማዉ።እግዚአብሄር ለአገልግሎት በምን መልኩ እንዳስታጠቀን እና የወንጌል መልእክታችንን እንዴት አድርገን ለተለያዩ አለማዊ ምልከታዎች ማዘጋጀት እንዳለብን መረዳት እና በእየሱስ ክርስቶስ ዉስጥ የሚገኘዉን የማይለወጠዉን የተስፋ ቃል እርሱን ለማያዉቀዉ ለእዚህ አለም ነዋሪዎች ለማድረስ ያግዘናል። . -
ሞዱል 6: ወንጌላዊነት እና አራቱ መንፈሳዊ ህግጋት
ይህ ስርአት በ ቢል ብርይት ለ ካምፓስ ክሩሴድ ለ ክርስቶስ የተጻፈዉን የአራቱን መንፈሳዊ ህግጋት ሃሳብ ጥቅም ላይ ያዉላል። ይህ ብልሃት የወንጌል አገልግሎታችንን ቅርጽ ለማስያዝ ጥቅም ላይ ልናዉለዉ እንችላለን። እንደ ወንጌል አገልግሎት መሳርያ እንጠቀምበት ዘንድ በመጽሃፍ መልክ ተዘጋጅቶ ይገኛል። ህትመት ላይ ሊዉል የሚችል የእዚሁ ትምህርት ቅጂ ከሚከተለዉ ድህረ ግጽ ላይ ሊገኝ ይችላል።www.4laws.com. ይህ ትምህርት አራቱን መንፈሳዊ ህግጋት ከማብራራቱም በላይ እንዴት አድርገን በዉይይት መልክ ወንጌልን ልናብራራ እንደምንችል እና ሰዎች እየሱስን እንደግል አዳኛቸዉ አድርገዉ እንዲቀበሉ መጋበዝ እንዳለብን ያሳየናል። ተግባራዊ ውይይቶች በዋናነት ተሳታፊ የሆኑ ሰዎችን ለተግባር እንዲነሱ ያበረታታል። -
ሞዱል 7: የክርስቲያን ሥነ-ምግባሮች
ይህ ተከታታይ ትምህርት የክርስትና ህይወት ስርአትን ያስተዋውቃል። ይህም ጸሎትን፣ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናትን እንዲሁም አይምሮአችን ዘላለማዊ የሆኑ ነገሮች ላይ እንዲያተኩር ማድረግን ይጨምራል። ይህ አስደሳች ርእስ በክርስትና ህይወት የጎለበቱ ሰዎችን የሚያበረታታ እና መንፈሳዊ ህይወታቸዉን እንዲያድሱ የሚያበረታታ ከመሆኑም በላይ አዳዲስ ክርስቲያኖችን ጥልቅ ወደሆነ እምነት ያመሩ ዘንድ ያግዛቸዋል። ይህ የትምህርት መሳርያ በተፈጥሮዉ ተግባራዊ ነዉ። ያም ሁኖ የሚያተኩረዉ ለእግዚአብሄር የተሰጠ ህይወት የሚያስገኘዉ መንፈሳዊ ጥቅሜታዎች ላይ ነዉ። -
ሞዱል 8: እግዚአብሄር እና መንፈሳዊ የእዉቀት ዘርፍ
ይህ ተከታታይ ትምህርት የጻድቅ እና ያሃጥያት ሃይሎች በአንድ ላይ የሚኖሩበትን የመንፈሳዊ አለም ሃቅ ይመረምራል። ይህ ሞዱል የሃጥያት ምንጭን ይመለከታል፣ የሰይጣንን የመጨረሻ ቅጣት ያመላክታል፣ የመንፈሳዊ የፍልሚያ መሳሪያዎችን ሃቅ እና በእለት ተእለት ህይወታችን ዉስጥ ጠንካራ ይዞታችንን ያሳያል። ከዚህም በላይ እግዚአብሄር የሰጠንን መሳርያዎች፣ እግዚአብሄር ሰይጣንን ለመፋለም ያቀደዉን ታላቅ የፍልሚያ እቅድ፣ በስተመጨረሻ እግዚአብሄር በሁሉም ነገሮች ላይ ስለሚኖረዉ የበላይነት እና እግዚአብሄር በህልም፣ ብራእይ እና በመላእክት አማካኝነት ከህዝቡ ጋር አልፎ አልፎ የሚገናኝበትን የመለከታዊ ሃይል መንገድ ያስተምራል።
የመንፈሳዊ አመራር መሰረቶች
የመንፈሳዊ አመራር መሰረቶች በተለይ ከአመራር ጋር የተያያዘ ትምህርትን ከክርስትያናዊ እይታ አንጻር እና አንድ ሰው መንፈሳዊ መሪነትን በተግባር የሚያከናውንባቸው የሕይወት መድረኮች ተመርኩዞ የሚሰጥ ነው። ለእዚህ ለመንፈሳዊ አመራር መሰረቶች ታሳቢ ተደራሾች ተደርገው የሚወሰዱት የክርስትና እምነት መሰረታዊ እውቀት እና ልምምድ ያላቸው እና በእምነቱ ውስጥ ሌሎችን መምራት የጀመሩ ክርስቲያኖች ናቸው። የመንፈሳዊ አመራር ልምምድ የሚደረገው በቤት ውስጥ፣ በስራ ቦታ፣ በትንንሽ ቡድኖች ውስጥ እና በደቀ መዝሙርነት ግንኙነቶች ውስጥ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚሰጡ መደበኛ ቦታዎች ላይ ማለትም በአስተማሪነት፣ በፓስተርነት፣ በሽማግሌነት ወይንም በዲያቆንነት ውስጥ ሊሆን ይችላል።
-
ሞዱል 1: ደቀ መዝሙርነት ሲመረመር
ይህ ተከታታይ ትምህርት የሚያጠናው የእየሱስ ክርስቶስ ተከታይ የሆኑትን መንፈሳዊ አወቃቀር ነው። ይሄዉም ደቀ መዝሙርነት ተብሎ የተጠቀሰው ሂደት ማለት ነው። የደቀ መዝሙርነት ሂደት የሚከሰተው አንድ ሰው በእየሱስ ክርስቶስ ማመን ከጀመረ፣ እግዚአብሄር ለህይወታቸው ባስቀመጠው እቅድ መሰረት የመኖር ፍላጎት ማሳደር ከጀመሩ በኋላ ነው። አዳዲስ አማኞች በእምነታቸው ያድጉ ዘንድ የማገዝን ስራ በሃላፊነት ስንቀበል በደቀ መዝሙርነት ልናሰለጥናቸው ጀመርን ማለት ነው። ይህ ግብአት ሌሎችን በደቀ መዝሙርነት ለማሰልጠን የሚፈልግ ማንኛውንም ሰው በተለይ ደግሞ ወንጌላዊነትን ለሚለማመዱ፣ ለአዳዲስ አማኞች ክትትል ለሚያደርጉ -
ሞዱል 2: አነስተኛ ቡድኖችን መምራት
ሞዱል 2፡ አነስተኛ ቡድኖችን መምራት የእዚህ ትምህርት አላማ በመጎልበት ላይ ያሉ መሪዎች በተሳካ መልኩ አነስተኛ ቡድኖችን መምራት ይችሉ ዘንድ በግንዛቤ እና በችሎታ የተሞሉ እንዲሆኑ ማስቻል ነው። ይህ አነስተኛ ቡድን ምናልባት የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን ወይንም የደቀ መዝሙርነት ቡድን ወይንም ደግሞ ለደቀ መዝሙርነት እና ለአገልግሎት የሚውል ማንኛውም አነስተኛ ቡድን ሊሆን ይችላል። ትኩረቱ በፍቅር እና በአገልግሎት ዝንባሌ የታጀበ ጠንካራ የሆነ የግንኙነት ችሎታን እና ገንቢ የሆኑን ግንኙነቶች ማዳበር ነው። የተሻለ የአነስተኛ ቡድን መሪ ለመሆን ራሰህን በበቂ መልኩ ያዘጋጀህ እንደሆነ ሌሎችን በደቀ መዝሙርነት የማሰልጠን እና የማስተማር ችሎታህን ማሳደግ ከማስቻሉም በላይ በተመሳሳይ ግዜ ለሁሉም ሰው በጣም የሚደሰትበትን ልምምድ ይፈጥራል። ይህ ሞዱል የተቀረጸው በአሁኑ ግዜ በቤተክርስቲያን አመራር ውስጥ ለሚያገለግሉ፣ በአነስተኛ ቡድኖች አመራር ውስጥ ላሉ ወይንም የአነስተኛ ቡድን አባል ለሆኑ ነው። የአነስተኛ ቡድን አባል የሆኑ ሰዎች አንድ ቀን እንዲህ ያሉ አነስተኛ ቡድኖችን የመምራት ሃላፊነትን ይረከባሉ የሚል ተስፋ አለ። -
ሞዱል 3: መንፈሳዊ ስጦታዎች
ሞዱል 3፡ መንፈሳዊ ስጦታ ይህ ሞዱል በቅዱሳት መጽሃፍት ውስጥ የተጠቀሱትን ሰፊ ሽፋን ያላቸውን መንፈሳዊ ስጦታዎች ከመመርመሩም በላይ አማኞች እነኚህን ስጦታዎች እንዴት አድርገው እግዚአብሄርን እና የእግዚአብሄርን ህዝቦች ለማገልገል እንደሚጠቀሙባቸው ይመለከታል። ተሳታፊዎች እነርሱ እና በእነርሱ አካባቢ ያሉ ሌሎች ያላቸውን መንፈሳዊ ስጦታ ለይተው ሊያውቁ የሚችሉበት መመሪያ ይሰጣቸዋል። ያላቸወን ስጦታ ጥቅም ላይ በማዋል፣ እርስ በእርስ አገልግሎትን በመሰጣጠት እና በመንፈስ እና በእውነት በማምለክ የእግዚአብሄርን አላማ እንዲያሟሉ ይበረታታሉ። -
ሞዱል 4: ቤተክርስቲያን እና አምልኮ
ሞዱል 4፡ ቤተክርስቲያን እና አምልኮ ይህ ተከታታይ ትምህርት የሚመረምረው ስለ ቤተክርስቲያን አላማ መጽሃፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምር እና የቤተክርስቲያን ህልውና እንዴት እንደጀመረ ነው። የቤተክርስቲያን መሪዎች እየሱስ ክርስቶስ እርሱ ወደ ሰማይ ባረገ ግዜ እርሱን በመወከል (በእዚህች አለም ላይ የእርሱ እንደራሴ በመሆን) በምድር ላይ ትሰራ ዘንድ ስለምን ቤተክርስቲያን እንደመሰረተ ጥልቅ የሆነ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል። በመንፈስ ቅዱስ ሃይል የተሞላችው ቤተክርስቲያን ወንጌልን በአለም ዙሪያ ታሰራጭ ዘንድ እና በአካባባቢ ማህበረሰብ ውስጥ እንድታገለግል ታዛለች። በተጨማሪም እግዚአብሔርን ለማምለክ ፣ በቃሉ ውስጥ ለመታዘዝ እና እርስ በእርሱ ለመደጋገፍና ለማበረታታት አባላቶቿ በየጊዜው ይገናኛሉ። -
ሞዱል 5: ቤተሰባዊ ህይወት
ሞዱል 5፡ ቤተሰባዊ ህይወት ይህ ተከታታይ ትምህርት የሚመለከተው ጤናማ ክርስቲያናዊ ቤተሰብን ለመመስረት መሰረት የሆነውን በቤት ውስጥ ያለን መንፈሳዊ አመራር ነው። ትምህርቱ የሚጀምረው መጽሃፍ ቅዱሳዊ መሰረት ስለቤተሰብ ያለውን ነገር ግንዛቤ የሚሰጥ ማዕቀፍን በማስቀመጥ ሲሆን አስከትሎም ቤተሰቦች የሚጋፈጧቸውን አንዳንድ ተግዳሮቶች ማለትም ለጋብቻ የሚደረግ ዝግጅት፣ ገንዘብን ማስተዳደር፣ ልጆችን መምራት እና ከትዳር አጋር ጋር መልካም የሆነ ግንኙነት መገንባት ወደመሳሰሉት ይሻገራል። ይህ ተከታታይ ትምህርት መንፈሳዊ አመራር ከቤት ይጀምራል። ይህንን አመራር በተመለከተም ወንዱም ይሁን ሴቷ የየራሳቸው የሆነ ልዩ የስራ ድርሻ ይኖራቸዋል የሚለውን አስተሳሰብ ይቀበላል። ይህ ትምህርት አሁን ባለንባት አለም ውስጥ ቤተሰቦች በተለያየ መልኩ ሊመጡ እንደሚችሉ እውቅና ቢሰጥም እግዚአብሄር ለቤተሰቦች ያለውን እጅግ ድንቅ የሆነ እቅድ ያቀርባል። ከእዚህ ትምህርት የሚያተርፉት በትዳር ላይ ያሉ፣ የወላጅነት የስራ ድርሻ ውስጥ ያሉ እንዲሁም ወደፊት ጤናማ ግንኙነት እንዲኖራቸው የሚመኙ ወጣቶች ናቸው። -
ሞዱል 6: የመሪዎች የህይወት ዘዬ
ሞዱል 6፡ የመሪዎች የህይውት ዘዬ ይህ ትምህርት የሚመረምረው ክርስቲያናዊ የአመራር የስራ ድርሻን ተቀብለው መስራት የሚችሉ ሰዎች የሚጠበቅባቸውን ተግባራዊ እና መንፈሳዊ ብቃት ነው። መሪ መሆን ማለት በተወሰኑ የሰዎች ስብስብ ፊት ቆሞ እኔን ተከተሉኝ ብሎ ከመጠየቅ እጅግ የዘለለ ነው! አንድ ሰው ታላቅ መሪ መሆን ይችል ዘንድ ማህበራዊ ይሁን ግላዊ ህይወቱ የተከበረ እና ከፍተኛ ደረጃን የጠበቀ ሊሆን ይገባል። ምንም እንኳን እያንዳንዳችን በተለያየ መንገድ ፈተናዎችን የምንጋፈጥ በሆንም መሪዎች ግን የተለየ ፈተናዎችን ነው የሚጋፈጡት። ይህ ሞዱል ከእነኚህ ፈተናዎች ውስጥ ጥቂቱን ለይቶ ከማውጣቱም በላይ እኒህን ፈተናዎች በምን መልኩ ሊወጡ እንደሚችሉ ለማሳየት በአመራር ዘርፍ የእግዚአብሄርን ጥሪ በመቀበል እርሱን ሲከተሉ ፈተናዎቹን እና ደስታዉን የመለማመድ እድል ከገጠማቸው ሰዎች ተግባራዊ ምክርን እንዲያገኙ ያግዛል። እያንዳንዱ ትህርት ከመሪዎች ለመሪዎች በሚል ገጽ ነው የሚጠቃለለው። በእዚህ ግጽ ላይ ከቀድሞ የክርስቲያን መሪዎች፣ በአሁን ግዜ ካሉ የክርስቲያን መሪዎች እና በእዚህ ርዕስ ላይ ሃሳባቸውን የሚያካፍሉ ሰዎችን (በአመራር ላይ የሌሉ ሰዎች) ከተናገሯቸው ላይ ይጠቅሳል። -
ሞዱል 7: ክርስቲያናዊ የባህሪ እድገት
ሞዱል 7፡ ክርስቲያናዊ የባህሪ እድገት ክርስቲያኖች ተደናቅፈው ከመንገዳቸው እንዲቀሩ እና አገልግሎቶች እንዳይሆኑ ሆነው ከአገልግሎት ውጭ እንዲሆኑ የሚያስገድዳቸው ዋንኛው ምክንያት በመሪዎች ውስጥ የሚስተዋሉ የባህሪ እድገት እጥረት ነው። አንድ ክርስቲያናዊ መሪ የሆነ ሰው የባህሪ እድገቶችን በቁም ነገር መመልከት ይኖርበታል። ምክንያቱም ደቀ መዝሙርነት በባህሪያችን ክርስቶስን ወደ መምሰል ማደግን ይጠይቃል እና ነው። ይህ ሞዱል አገልጋይ የሆነን መሪ ለማጎልበት አስፈላጊ የሆኑ በርካታ ክርስቲያናዊ ባህሪያትን ይመረምራል። ስለ እነዚህ ባህሪያት መጽሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን እና እየሱስ እና ሌሎች ላይ እነኚህ ባህሪያት እንዴት እንደሚንጸባረቁ እንመለከታለን። አምላካዊ የሆና ባህሪ የክርስቶስ ተከታይ በሆነ በእያንዳንዱ ሰው ህይወት ላይ በተለይ ደግሞ ሌሎችን በሚመሩት ላይ በግልጽ የሚታይ መሆን አለበት። -
ሞዱል 8: ይቅርታ እና እርቅ
ሞዱል 8፡ ይቅርታ እና እርቅ በህይወታችን ውስጥ የእግዚአብሄርን ይቅርታ መቀበል እና ለሌሎች ይቅርታን መለገስ አዳጋች ነገር ሊሆን ይችላል። ሌሎችን ይቅር ማለት በተፈጥሯችን ማድረግን እንሻ ዘንድ ከምንወደው በተቃራኒ የሚሄድ ነገር ነው። ነገር ግን እግዚአብሄር ልባችንን እና አእምሮአችንን ይቀይር ዘንድ በፈቀድን ግዜ ከእግዚአብሄር ጋር እና እርስ በእርሳችን እርቅን መለማመድ ልንጀምር እንችላለን። ይህ ሞዱል የሚመረምረው የይቅርታን መጽሃፍ ቅዱሳዊ መሰረት፣ ለእርቅ የሚያስፈልገውን ሂደት እና እርስ በእርስ በሰላም መኖርን እንዴት አድርጎ ማስተዋወቅ እንደሚቻል ነው። ከእዚህም በተጨማሪ በግለሰቦች መካከል ወይንም ደግሞ በማህበረሰን አባላት መካከል ሊያስፈልግ የሚችለውን ይቅርታ ይመረምራል። -
ሞዱል 9: ክርስቲያናዊ አስተምህሮ
ሞዱል 9፡ ክርስቲያናዊ አስተምህሮ ይህ ተከታታይ ትምህርት በአብዛኛው ግዜ ስህተት ለሚፈጸምባቸው ቦታዎች እና ይህ ስህተት እውነተኛ እምነት ላይ ለሚያደርሰው ተጽእኖ ትኩረትን በመስጠት የእምነታችን መሰረት የሆኑትን አስተምህሮዎች የሚመረምር ትምህርት ነው። አስተምህሮ ማለት እምነታችንን እንዴት መለማመድ እንዳለብን አቅጣጫ እንይዝ ዘንድ የሚያግዘን በውስጣችን ያለ የእምነቶች ስብስብ ነው። ክርስቲያኖች ስለ እግዚአብሄር ተፈጥሮ እና ስለ እኛ ድህነት በተለይ ደግሞ በማስተማር ላይ እና ደቀ መዛሙራንን በማሰልጠን ላይ የተሰማሩ እንደሆነ ትክክለኛ እምነት እንዲኖራቸው ያስፈልጋል። ይህ ሞዱል ቅዱሳን መጻህፍትን በእየአንዳንዱ ረዕስ ላይ በመመርመር በእየአንዳንዱ አስተምህሮ ላይ ስህተቶች እና ግራ መጋባቶች የት ላይ እንደሚፈጠሩ ይመረምራል። -
ሞዱል 10: ስለ ፓስተርነት መሰረታዊ ሃሳቦች
ሞዱል 10፡ ስለ ፓስተርነት መሰረታዊ ሃሳቦች ይህ ሞዱል ስልጠና ሳይወስዱ በአጥቢያ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ በፓስተርነት ለሚያገለግሉ መሪዎች፣ ፓስተርን ለሚፈልጉ የቤተክርስቲያን ስብስቦች ወይንም በፓስተርነት ማገልገል የሚሹ ክርስቲያኖችን ታሳቢ በማድረግ በተለይ የ ፓስተርነት መሰረታዊ ሃሳቦች ላይ የሚያተኩሩ ረዕሶችን ይመለከታል። አንድ ፓስተር በአጥቢያ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ስለሚኖሩት በርካታ ሃላፊነቶች ከመመልከታችንም ባሻገር የቤተክርስቲያን አባላት ከፓስተሮቻቸው ምን ሊጠብቁ እንደሚገባም ይመለከታል። ይህ ሞዱል የቤተክርስቲያን ልዩ የሆኑ ፍላጎቶችን ማለትም በተለያዩ የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉን ማገልገልን እና የቤተክርስቲያን እድገትን ከኝዛቤ ማስገባትንም ያካትታል።
ማንነታችን በክርስቶስ
የእዚህ ትምህርት አላማ ክርስቲያኖች በክርስቶስ ማንነታቸዉን መጽሃፍ ቅዱሳዊ መሰረቱን ማብራራት እና የህንን ማንነት በግልጽ የመረዳትን ጠቀሜታ መረዳት ነዉ።
የእግዚአብሔር ጸጋ
ክርስቲያኖች እንዴት የእግዚአብሄርን ሞገስ ሊቀበሉ እንደሚችሉ ማብራራት እና ይህ ሞገን ከእግዚአብሄር ጋር እና ከሌሎች ጋር ያለንንዝምድና ላይ ምን አይነት ተጽእኖ እንደሚያሳድር መመልከት።
እግዚአብሔርን መዉደድ
የእዚህ ትምህርት አላማ እግዚአብሄርን በሙሉ ልብህ ፣ ነፍስህ፣ አእምሮህ እና ጥንካሬህ ትወደዉ ዘንድ የሚያዘዉን ተዛዝ መረዳት ነዉ።
ዓለምን በወንጌል የመድረስ ጥሪ
ተሳታፊዎች ስለእየሱስ በአካቢያቸዉ ያሉትን ሁሉ እንዲደርሱ እና እስከአሁን የማያምኑ ሰዎች ሲያጋጥሙዋቸዉ ወንጌልን የሚያካፍሉበትን አጋጣሚ ለመፍጠር የሞክሩ ዘንድ ይፈተናሉ።
እግዚአብሄር ድል አድራጊ ነዉ
የእዚህ ትምህርት አላማ እግዚአብሄር በሰይጣን ላይ ድልን እንደሚቀዳጅ እና በሁሉም ነገሮች ላይ የበላይ እጅ እንዳለዉ መመልከት ነዉ። ተሳታፊዎች በእግዚአብሄር ስለሚገኝ ነጻነት መጽሃፍ ቅዱስ የሚለዉን ይመለከታሉ።
- እየሱስ ክርስቶስ ማን ነዉ?
- ድነትን መረዳት
- የክርስቲያን ሕይወት እና የአለም ዕይታ
- ከእግዚአብሄር ጋር ያለን ዝምድና
- የወንጌል ስርጭት መንደርደርያ
- ወንጌላዊነት እና አራቱ መንፈሳዊ ህግጋት
- የክርስቲያን ሥነ-ምግባሮች
- እግዚአብሄር እና መንፈሳዊ የእዉቀት ዘርፍ
- ደቀ መዝሙርነት ሲመረመር
- አነስተኛ ቡድኖችን መምራት
- መንፈሳዊ ስጦታዎች
- ቤተክርስቲያን እና አምልኮ
- ቤተሰባዊ ህይወት
- የመሪዎች የህይወት ዘዬ
- ክርስቲያናዊ የባህሪ እድገት
- ይቅርታ እና እርቅ
- ክርስቲያናዊ አስተምህሮ
- ስለ ፓስተርነት መሰረታዊ ሃሳቦች