መጽሐፈ መክብብ
መጽሐፈ ኢዮብ
ሕይወት ፍትሓዊ ሳትሆን ስትቀር እና ያለ በቂ ምክንያት በመከራ ውስጥ በሚያልፉበት ጊዜ፣ እግዚአብሔርን እንዴት መታመን ይችላሉ? የኢዮብ ታሪክ፣ እግዚአብሔር ዓለምን በጥበብ ይመራል ማለት ምን እንደ ሆነ እና ይህ እውነት በክፉ ጊዜ ሰላምን እንዴት እንደሚያመጣ እንድናስብ ይጋብዘናል። መጽሐፈ ኢዮብ ጥበብን የተመለከቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦችን ከሚዳስሱ ሦስት መጻሕፍት መካከል የመጨረሻው ነው። #BibleProject #Bible #መጽሐፈ ኢዮብ የቪዲዮ ምስጋናዎች የአማርኛ ፕሮዳክሽን ቡድን BETE-SEMAY Creative Media Addis Ababa, Ethiopia ኦሪጅናል የእንግሊዘኛ ይዘትና ፕሮዳክሽን BibleProject ፖርትላንድ፣ ኦሬገን፣ ዩ.ኤስ.ኤ
መጽሐፈ ምሳሌ
መጽሐፈ ምሳሌ እግዚአብሔርን በሚፈሩ ትውልጆች እና የጥበብ ሰዎች የተደራጀ የጥበብ መጽሐፍ ነው። በመልካምነት የተሞላ ሕይወት እንዲላበሱ፣ በጎነት እና እግዚአብሔርን የመፍራት ሕይወት እንዲኖርዎ ያበረታታዎታል። መጽሐፈ ምሳሌ መሰል መጽሐፍ ቅዱሳዊ የጥበብ ጭብጦችን ከሚዳስሱ ሦስት መጻሕፍት መካከል አንዱ ነው። #BibleProject #Bible #መጽሐፈ ምሳሌ
የከተማ ፋይዳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ (እና እግዚአብሔር ለከተማ ያለው እቅድ)
በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ በቃየን ከተገነባችው የመጀመሪያዋ ከተማ ጀምሮ፣ በአዲሱ ፍጥረት ውስጥ የመጨረሻዋ የአትክልት ከተማ እስከሆነችው እስከ ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም ድረስ የከተማን ጭብጥ ይመርምሩ። በዚህ ቪዲዮ የሚከተሉትን ይማራሉ፦ - ከተማን ከተማ የሚያደርገው ምን እንደ ሆነ - የመጀመሪያው ከተማ ለምን እንደ ተሠራ - የባቢሎን እና የእግዚአብሔር ከተማ ያላቸው ተቃርኗዊ ሥነ ምግባር - እግዚአብሔር የአትክልት ስፍራውን ወደ ከተማዋ ለማምጣት ያለው ያልተጠበቀ ዕቅድ - ሰማያዊቷ ከተማ ወደ ምድር ስትመጣ ምን እንደምትመስል መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ኢየሱስ የሚመራ ወጥነት ያለው ታሪክ እንደ ሆነ ሰዎች እንዲገነዘቡ የሚያግዙ ተጨማሪ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን እና የፖድካስት ዝግጅቶችን ለማግኘት ሙሉውን ቻናላችንን ይመልከቱ። #BibleProject #Bible #ከተማ
የሕይወት ዛፍ
በመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያዎቹ ገጾች ውስጥ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ስጦታ ሰጥቷቸዋል፤ ይህን ሥጦታ ሰዎች በጥፋታቸው ምክንያት ወዲያውኑ ያጡት ሲሆን፣ ስጦታውም የሕይወት ዛፍን በመብላት የሚገኝ የዘላለም ሕይወት ነበር። በዚህ ቪዲዮ፣ የዚህን ብርቱ መልእክት ያለውን ምስል ትርጕም እና በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ የተቀደሱ ዛፎች የሚጫወቱትን ቍልፍ ሚና እንመረምራለን። ይህ ምስል ለሰው ልጆች ሁሉ አዲስ የሕይወት ዛፍ ይሆን ዘንድ በዕንጨት ላይ ወደ ሞተው ኢየሱስ የሚመራን ነው። #BibleProject #Bible #የሕይወት ዛፍ የቪዲዮ ምስጋናዎች የአማርኛ ፕሮዳክሽን ቡድን BETE-SEMAY Creative Media Addis Ababa, Ethiopia ኦሪጅናል የእንግሊዘኛ ይዘትና ፕሮዳክሽን BibleProject ፖርትላንድ፣ ኦሬገን፣ ዩ.ኤስ.ኤ
ፍትሕ
በዛሬው ዓለም ውስጥ ፍትሕ እጅግ ተፈላጊ እና አጨቃጫቂ ርእሰ ጕዳይ ነው። ነገር ግን ፍትሕ ምንድን ነው? ብይን የሚሰጠውስ ማን ነው? በዚህ ቪዲዮ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን የፍትሕ ጭብጥ እንመረምራለን፤ እንዲሁም ፍትሕ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ ሥር የሰደደ ፅንሰ ዐሳብና ወደ ኢየሱስ የሚመራን መሆኑን እንቃኛለን። #BibleProject #Bible #ፍትሕ
ቅድስና
በዚህ ቪዲዮ የእግዚአብሔር ቅድስና በሰው ልጆች ላይ ስለሚያመጣው ተቃርኖ እንመረምራለን። እግዚአብሔር ፍጹም የተለየ፣ የእውነት ሁሉ ፈጣሪ እና የመልካምነት ሁሉ ደራሲ ነው። ሆኖም ግን፣ ይህ የእግዚአብሔር መልካምነት ለሟች እና ለምግባረ ብልሹ ሰዎች አደገኛ ሊሆን ይችላል። በመጨረሻም፣ ይህ ተቃርኖ የተፈታው ፍጥረቱን ለመፈወስ በመጣውና የእግዚአብሔር ቅድስና መገለጫ በሆነው በኢየሱስ ነው። #BibleProject #Bible #ቅድስና
የእግዚአብሔር አምሳል
ይህ በእግዚአብሔር አምሳል ላይ ትኵረቱን ያደረገው ቪዲዮ፣ ምድርን እና በውስጧ ያሉትን እንዲያለሙ እና ወደ አዲስ አድማስ እንዲወስዷቸው ተልእኮ የተሰጣቸው ከእግዚአብሔር ጋር ዐብረው የሚገዙ ሰዎችን ዕሳብ ይመረምራል። ይህ የከበረ ጥሪ በራስ ወዳድነታችን እና በክፋታችን የተሸረሸረው እንዴት ነው? ኢየሱስ በሕይወቱ፣ በሞቱና በትንሣኤው አማካኝነት ሰው ለመሆን የሚያስችለንን አዲስ መንገድ የከፈተልንስ እንዴት ነው? #BibleProject #Bible #የእግዚአብሔር አምሳል
መንፈስ ቅዱስ
በዚህ ቪዲዮ፣ “መንፈስ” የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ፅንሰ ዐሳብ ቀዳሚ ፍቺ እንመረምራለን፤ በተጨማሪም የእግዚአብሔር መንፈስ በፍጥረት ሁሉ ውስጥ መገኘቱ ምን ማለት እንደ ሆነ እንመለከታለን። በመጨረሻም፣ መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ በኩል ተገለጦ አዲስ ፍጥረትን ለማምጣት ወደ ተከታዮቹ ሕይወት ተልኳል። #BibleProject #Bible #መንፈስ ቅዱስ
የስደት መንገድ
የኢየሱስ ተከታዮች ለእግዚአብሔር መንግሥት ሙሉ በሙሉ ታማኝ መሆን ከፈለጉ፣ በዘመናቸው ካሉ መንግሥታትና የሥልጣን መዋቅሮች ጋር እንዴት ያለ ግንኙነት ሊኖራቸው ይገባል? በዚህ ቪዲዮ ዳንኤል እና ጓደኞቹ በባቢሎን ግዞት ሳሉ ያሳለፉት ተሞክሮ፣ ውጥረቱን ለመመርመር የሚሰጠንን ጥበብ እንመለከታለን። በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢየሱስን መከተል ማለት የስደትን መንገድ መማር ማለት ነው። #BibleProject #Bible #የስደት መንገድ
ዘላለማዊ ሕይወት
ኢየሱስ ለሰዎች የዘላለም ሕይወትን ይሰጣል፤ ሆኖም ግን የዘላለም ሕይወት ምን ማለት ነው? አሁን እና በሚመጣው ዘመን ወደ እግዚአብሔር ሕይወት የሚጋብዘንን የዚህን ሐረግ ፍቺ ይመርምሩ። #BibleProject #Bible #ዘላለማዊ ሕይወት