መሥዋዕት እና ስርየት

እግዚአብሔር መልካም ከሆነው የእርሱ ዓለም ውስጥ፣ እኩይንና ተጽዕኖዎቹን በማስወገድ ተልእኮ ላይ ነው። ይሁን እንጂ፣ ይህን ሲያደርግ ሰዎችን እስከወዲያኛው በሚያጠፋ መልኩ እንዲሆን አይሻም። በዚህ መሥዋዕትን እና ስርየትን በሚመለከት በተዘጋጀ ቪዲዮ፣ እግዚአብሔር የሰውን ክፋት በእንስሳት መሥዋዕትነት አማካኝነት “የሚሸፍንበትን” ጭብጥ እንዲሁም ይህ እንዴት ወደ ኢየሱስ፣ ወደ ሞቱ እና ትንሣኤው እንደሚጠቁም እንመለከታለን። #BibleProject #Bible #መሥዋዕት እና ስርየት …ንባብ ጨምር

ሕግ

በዚህ ቪዲዮ፣ በብሉይ ኪዳን የሚገኙትን ጥንታዊ ሕጎች አስፈላጊነትን እንመረምራለን። ሕጎቹ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ለምንድን ነው? ለኢየሱስ ተከታዮችስ የሚያስተላልፉት መልእክት ምንድን ነው? ‘እግዚአብሔርን ውደድ፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ’ ወዳለው፣ ለሕጉ ፍጻሜንና መደምደሚያን ወደ ሰጠው ወደ ኢየሱስ የሚያመራውን፣ በአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቍልፍ ታሪክ አማካኝነት ሕጎቹ አንድ ስልታዊ ዐላማን እንዴት እንዳሳኩ የምንምለከት ይሆናል። #BibleProject #Bible #ሕግ

መሲሕ

በዚህ መሢሑን በሚመለከት በተዘጋጀው ቪዲዮ፣ በመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ፣ ሦስተኛው ምዕራፍ ላይ የሚገኝን ምስጢራዊ ተስፋ እንመለከታለን። ይህም ተስፋ አንድ ቀን እኩይን ስለሚጋፈጥ እና የሰው ልጆችን #BibleProject #Bible #መሲሕ

እግዚአብሔር

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጸውን እግዚአብሔር መረዳት ቀላል አይደለም፤ ነገር ግን ልንረዳ በማንችለው ውስጥ የተሻለ መረዳት ብናገኝስ? በዚህ ቪዲዮ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ የተገለጸውን የእግዚአብሔርን ውስብስ #BibleProject #Bible #እግዚአብሔር

ዳሰሳ፡- 1ኛ-2ኛ ዜና መዋዕል

የመጽሃፉን ንድፍ እና የሃሳብ ፍሰት የሚያብራራውን በ1ኛ-2ኛ ዜና መዋዕል ላይ የሰራነውን የዳሰሳ ቪዲዮ ይመልከቱ። መጽሃፈ ዜና ሙሉውን የብሉይ ኪዳን ታሪክ ዳግም ይተርካል፣ እንዲሁም የመሲሁ ንጉስ የወደፊት ተስፋን እና የቤተ መቅደስን መታደስ አጉልቶ ያሳያል። #BibleProject #Bible #ዜና መዋዕል

ዳሰሳ፡- ዕዝራ-ነህምያ

የመጽሃፉን ንድፍ እና የሃሳብ ፍሰት የሚያሳየውን በዕዝራ እና ነህምያ ላይ የሰራነውን የዳሰሳ ቪዲዮ ይመልከቱ። ዕዝራ እና ነህምያ ላይ፣ ብዙ እስራኤላውያን ከምርኮ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ እናያለን፣ በዚያም ከብዙ መንፈሳዊ እና የሞራል ውድቀቶች ጎን ለጎን አንዳንድ ስኬት ይገጥማቸዋል። #BibleProject #Bible #ዕዝራ-ነህምያ

ዳሰሳ፡- ትንቢተ ዳንኤል

የመጽሃፉን ንድፍ እና የሃሳብ ፍሰት የሚያሳየውን በትንቢተ ዳንኤል ላይ የሰራነውን የዳሰሳ ቪዲዮ ይመልከቱ። የትንቢተ ዳንኤል ታሪክ ምንም እንኳን በባቢሎን ምርኮ ውስጥ ቢሆንም ታማኝነትን ያነቃቃል። ራዕዮቹ እግዚአብሔር ትውልድን ሁሉ በራሱ ህግ ስር እንደሚያስገዛ ተስፋን ይሰጣሉ። #BibleProject #Bible #ትንቢተ ዳንኤል

ዳሰሳ፡- አስቴር Esther

የመጽሃፉን ንድፍ እና የሃሳብ ፍሰት የሚያሳየውን አስቴር ላይ የሰራነውን የዳሰሳ ቪዲዮ ይመልከቱ። መፅሀፈ አስቴር እግዚአብሔርንም ሆነ ስራውን ሳይጠቅስ፣ እግዚአብሔር ህዝቡን ከጥፋት ለመታደግ በምርኮ ምድር ያሉ ሁለት እስራኤላውያንን እንዴት እንደተጠቀመ ይገልፃል። #BibleProject #Bible #አስቴር

ዳሰሳ፡- ሰቆቃወ ኤርምያስ

የመጽሃፉን ንድፍ እና የሃሳብ ፍሰት የሚያሳየውን ሰቆቃወ ኤርምያስ ላይ የሰራነውን የዳሰሳ ቪዲዮ ይመልከቱ። ሰቆቃወ ኤርምያስ ኢየሩሳሌም በባቢሎን ከወደመች በኋላ የቀረቡ የአምስት የሀዘን ግጥሞች ስብስብ ነው። #BibleProject #Bible #NameOfVideo

ዳሰሳ፡- መክብብ

የመጽሃፉን ንድፍ እና የሃሳብ ፍሰት የሚያሳየውን መክብብ ላይ የሰራነውን የዳሰሳ ቪዲዮ ይመልከቱ። ይህ መጽሐፍ ሞትን እና የዘፈቀደ እድልን፣ እንዲሁም እነዚህ ነገሮች በእግዚአብሔር ቸርነት ላይ ባለ የየዋህነት እምነት ላይ የሚያደርሱትን ችግሮች እንድንጋፈጥ ያስገድደናል። #BibleProject #Bible #መክብብ

ዳሰሳ፡- ሩት

የመጽሃፉን ንድፍ እና የሃሳብ ፍሰት የሚያብራራውን ሩት ላይ የሰራነውን የዳሰሳ ቪዲዮ ይመልከቱ። ሩት ላይ፣ አንድ እስራኤላዊ ቤተሰብ አሳዛኝ የሆነ ሞት ይገጥመዋል፤ እግዚአብሔርም በዳዊት ዘር ላይ ተሃድሶን ለማምጣት አንዲት እስራኤላዊ ያልሆነችን ሴት ታማኝነት ይጠቀማል። #BibleProject #Bible #ሩት