መንፈስ ቅዱስ
የስደት መንገድ
የኢየሱስ ተከታዮች ለእግዚአብሔር መንግሥት ሙሉ በሙሉ ታማኝ መሆን ከፈለጉ፣ በዘመናቸው ካሉ መንግሥታትና የሥልጣን መዋቅሮች ጋር እንዴት ያለ ግንኙነት ሊኖራቸው ይገባል? በዚህ ቪዲዮ ዳንኤል እና ጓደኞቹ በባቢሎን ግዞት ሳሉ ያሳለፉት ተሞክሮ፣ ውጥረቱን ለመመርመር የሚሰጠንን ጥበብ እንመለከታለን። በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢየሱስን መከተል ማለት የስደትን መንገድ መማር ማለት ነው። #BibleProject #Bible #የስደት መንገድ
ዘላለማዊ ሕይወት
ኢየሱስ ለሰዎች የዘላለም ሕይወትን ይሰጣል፤ ሆኖም ግን የዘላለም ሕይወት ምን ማለት ነው? አሁን እና በሚመጣው ዘመን ወደ እግዚአብሔር ሕይወት የሚጋብዘንን የዚህን ሐረግ ፍቺ ይመርምሩ። #BibleProject #Bible #ዘላለማዊ ሕይወት
የሰው ልጅ
“ክርስቶስ” የኢየሱስ የመጨረሻ ስም ወይም ለራሱ የሰጠው የማዕረግ ስም የሚመስልዎ ከሆነ፣ እንደገና ቈም ብለው ማሰብ ይኖርብዎታል! ኢየሱስ ራሱን ለመግለጽ ብዙውን ጊዜ ይጠቀምበት የነበረው ስም፣ “የሰው ልጅ” የሚል ነው። በዚህ ቪዲዮ፣ የዚህን አስደናቂ መጠሪያ ሐረግ ትርጕም እንመረምራለን፤ ይህም እንዴት ወደ ትልቁ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እንዴት እንደሚመራን እንመለከታለን። #BibleProject #Bible #የሰው ልጅ
የጌታ ቀን
እግዚአብሔር በዓለም ላይ ሰዎች ለሚፈጽሟቸው እኩይ ተግባራት ግድ ይለዋልን? ግድ የሚለው ከሆነ ምን እያደረገ ነው? በዚህ “የጌታ ቀን” በተሰኘ ቪዲዮ፣ እግዚአብሔር የሰውን እኩይ ተግባር የሚጋፈጥባቸውን የተለያዩ መንገዶች፣ እንዲሁም ከዚህ እኩይ ጀርባ ያለውን ጥልቅ መንፈሳዊ ክፋት እንመረምራለን። በመጨረሻ፣ ኢየሱስ ይህን የታሪክ ሴራ እንዴት ወደ ፍጻሜ እንዳመጣው እና እኩዩ እንዲያሸንፈው በመፍቀድ፣ እንዴት እንደረታው እንመለከታለን። #BibleProject #Bible #የጌታ ቀን
የመንግሥቱ ወንጌል
በዚህ ቪዲዮ “ወንጌል” ስለተሰኘው ቃል አመጣጥና፣ ቃሉ የብሉይ ኪዳንን ታሪክ ከኢየሱስ ታሪክና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ካወጀው ታሪክ ጋር እንዴት እንደሚያያዝ እንመለከታለን። ኢየሱስ የእግዚአብሔርን አገዛዝ እና ንግሥና ወደዚህ ዓለም ያመጣው ባልተጠበቀ መንገድ ነው፤ ይህም እንዲሰሙ ከሚመኙት እጅግ የላቀው የምሥራች ነው። #BibleProject #Bible #የመንግሥቱ ወንጌል
ዘንዶዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ፤ እነሆ ምክንያቱ፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች፣ ፍጥረትን ለሥርዐት አልቦነት እና ሞት የሚዳርጉትን መንፈሳዊ ኀይሎች ለመግለጽ የዘንዶ ምስልን እንዴት እንደተጠቀሙ ይመርምሩ። በዚህ ቪዲዮ ውስጥ የሚከተሉትን ይማራሉ፡- - ዘንዶዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ መቼ እንደተገለጹ - ሰዎች እና መንግሥታት እንዴት እንደ ዘንዶ ሊመስሉ እንደሚችሉ - ዘንዶ ገዳዮች እንዴት ወደ ዘንዶው ኃይል ሊሳቡ እንደሚችሉ - ኢየሱስ አስደናቂ በሆነ መንገድ ዘንዶውን እንዴት እንደተቋቋመውና እና እንዳሸነፈው መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ኢየሱስ የሚመራ ወጥነት ያለው ታሪክ እንደ ሆነ ሰዎች እንዲገነዘቡ የሚያግዙ ተጨማሪ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን እና የፖድካስት ዝግጅቶችን ለማግኘት ሙሉውን ቻናላችንን ይመልከቱ። #BibleProject #Bible #ዘንዶ
ኪዳናት
መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ጋር ያለውን ግንኙነት የሚገልጽበት ዋና መንገድ የአጋርነት ምስልን በመጠቀም ነው። ይህ ቃል ኪዳንን የተመለከተው ቪዲዮ፣ እግዚአብሔር የቃል ኪዳን አጋር ቁንጮ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ዓለምን ይታደግ ዘንድ ከተለያዩ የሰው አጋሮች ጋር በተከታታይ የመሠረታቸውን መደበኛ ግንኙነቶች የሚያሳይ ነው። #BibleProject #Bible #ኪዳናት
ሰማይ እና ምድር
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሰማይ ምን ያስተምራል? ሰማይ ከምድር ጋር ያለው ግንኙነትስ ምንድን ነው? በዚህ ቪዲዮ፣ ሰማይ እና ምድር እንዲገናኙ ታስቦ እንደ ነበር የሚያሳየውን አስገራሚ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አመለካከት፣ እንዲሁም ኢየሱስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሁለቱን አንድ ላይ ለማምጣት ተልእኮ ላይ መሆኑን እንቃኛለን። #BibleProject #Bible #ሰማይ እና ምድር
መሥዋዕት እና ስርየት
እግዚአብሔር መልካም ከሆነው የእርሱ ዓለም ውስጥ፣ እኩይንና ተጽዕኖዎቹን በማስወገድ ተልእኮ ላይ ነው። ይሁን እንጂ፣ ይህን ሲያደርግ ሰዎችን እስከወዲያኛው በሚያጠፋ መልኩ እንዲሆን አይሻም። በዚህ መሥዋዕትን እና ስርየትን በሚመለከት በተዘጋጀ ቪዲዮ፣ እግዚአብሔር የሰውን ክፋት በእንስሳት መሥዋዕትነት አማካኝነት “የሚሸፍንበትን” ጭብጥ እንዲሁም ይህ እንዴት ወደ ኢየሱስ፣ ወደ ሞቱ እና ትንሣኤው እንደሚጠቁም እንመለከታለን። #BibleProject #Bible #መሥዋዕት እና ስርየት
ሕግ
በዚህ ቪዲዮ፣ በብሉይ ኪዳን የሚገኙትን ጥንታዊ ሕጎች አስፈላጊነትን እንመረምራለን። ሕጎቹ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ለምንድን ነው? ለኢየሱስ ተከታዮችስ የሚያስተላልፉት መልእክት ምንድን ነው? ‘እግዚአብሔርን ውደድ፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ’ ወዳለው፣ ለሕጉ ፍጻሜንና መደምደሚያን ወደ ሰጠው ወደ ኢየሱስ የሚያመራውን፣ በአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቍልፍ ታሪክ አማካኝነት ሕጎቹ አንድ ስልታዊ ዐላማን እንዴት እንዳሳኩ የምንምለከት ይሆናል። #BibleProject #Bible #ሕግ